መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 15፤2014-በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ከ70 ሺህ በላይ የቁም ከብቶች መሞታቸው ተገለጸ

በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ከ70 ሺህ በላይ የቁም ከብቶች መሞታቸው ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ችግሩ ምንም እንኳን አስከፊ ቢሆንም እስካሁን ድረስ በሰዎች ላይ ጉዳት ባይደርስም ከ70 ሺህ በላይ የቁም ከብቶች ሞተዋል።መጪው ጊዜ ዝናብ የሚጠበቅበት ባላመሆኑ ችግሩ በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት እንደሆነባቸው ተገልጿል ።

ድርቁ የተከሰተው በሁለት ምክንያቶች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን አንደኛው በቦረና አካባቢ ከመጋቢት 15 ጀምሮ መዝነብ የነበረበት በአካባቢው አጠራር ገና ተብሎ የሚጠራው የአካባቢውን 70 በመቶ የሚሆነውን የውሃ ፍላጎት የሚሸፍነው ዝናብ በ2013 ዓ.ም በወቅቱን ጠብቆ ሳይዘንብ በመቅረቱ የተነሳ ነው።

እንዲሁም ሁለተኛው መንስዔ የአካባቢውን 30 በመቶ የሚሆነውን የውሃ ፍላጎት የሚሸፍነው ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ወቅቱን ጠብቆ ከመሰከረም 15 ጀምሮ ባለመዝነቡ መሆኑን የክልሉ የጥናት እና ምርምር ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ከተማው ኡርጋ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

በቦረና አካባቢ ከ2 ሚሊዮን በላይ እንስሳቶች የሚገኙ ሲሆን በአሁን ወቅት ግን ለመኖ የሚሆን ቀለብ የተወደደ በመሆኑ በቀላሉ እንስሳቶቹን መመገብም አዳጋች እንደሆነባቸው አያይዘው አቶ ከተማው ኡርጋ ገልጸዋል።

በመሆኑም የችግሩ አሳሳቢነት እየበረታ የመጣ በመሆኑ የህብረተሰቡ ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ የሚያስፈልግ ሲሆን በሃገር ውስጥ ሆነ ከሃገር ውጪም ያለ ማንኛውም አካል ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ የፊንፊኔ ዙሪያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ኤሊያስ ሙኔ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *