መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 15፤2014-ጠ/ሚ ዐቢይ ከትናንት ጀምሮ በግንባር አመራር እየሰጡ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከትናንት ጀምሮ በግንባር አመራር እየሰጡ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ!

ከኢትዮጵያ የሚበልጥ ነገር ባለመኖሩም መሪዎችና ህዝቡ በጋራ መተባበራቸውን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ ነው።

በመግለጫቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ከትናንትና ጀምሮ በግንባር አመራር እየሰጡ መሆኑን ገልጸዋል።ሌሎች አመራሮችም የህልውና ዘመቻውን በመቀላቀል ወደ ግንባር መዝመታቸውን ነው የገለጹት፡፡

መደበኛ ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እየተመራ መሆኑን ጠቅሰዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመታቸው በርካቶችን ያነቃቃና በርካቶች እንዲከተሏቸው አድርጓልም ብለዋል ዶክተር ለገሰ።የጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመት የአመራር ብቃታቸውንና የቆየ የአይበገሬነት ታሪክ ያሳያልም ነው ያሉት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *