መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 16፤2014-የሀይማኖት ተቋማት የአሸባሪዉን ቡድን ሰይጣናዊ ተግባር ማጋለጥና ማዉገዝ እንደሚገባቸው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

የሀይማኖት ተቋማት የአሸባሪዉን ቡድን ሰይጣናዊ ተግባር ማጋለጥና ማዉገዝ እንደሚገባቸው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ

የአዲስአበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባዘጋጀው የዉይይት መድረክ ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተገኝተዋል።

ከንቲባዋ አሁን የገጠመን ዘርፈ ብዙ ጦርነት በፖለቲካ ሀሳብ ልዩነት ሳይሆን ኢትዮጵያን የማፍረስ፣ እንደ አገር ፀንተን እንዳንቆም የተጋረጠብን አደጋ ነዉ ብለዋል።

አሸባሪዉና ወራሪዉ የህወኃት ቡድን ከታሪካዊ ጠላቶቻችን እና ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን የደቀነብንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ የሀይማኖት ተቋማት ሚና አይተኬ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

አሸባሪዉ ቡድን ባለፉት 27 አመታት ዉስጥ በቤተ እምነቶች ዉስጥ በዘረጋው የራሱ ጉዳይ አስፈፃሚ ቡድን ቤተ እምነቶችን ከዓላማቸው ዉጪ ለጥፋት ተልዕኮው ማስፈፀሚያ ሊጠቀምባቸዉ መሞከሩን አንስተዋል።

በወራሪነት በያዛቸው አካባቢዎችም ቤተ እምነቶችን ሲዘርፍና ሲያወድም፣ የሀይማኖት አባቶችን ሲገድልና ሲያዋርድ ታይቷል ፤ አንዳንድ የሀይማኖት አባቶች ተብዬዎችም ለጥፋት ተልዕኮው ማስፈፀሚያ ሆነው በዓለም አደባባይ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያንን ሲረግሙ ሰምተን አፍረናል ብለዋል።

የሀይማኖት ተቋማት ይህንን ሴራ በንቃት መከታተልና የአሸባሪዉን ቡድን ሰይጣናዊ ተግባር ማጋለጥና ማዉገዝ እንደሚገባቸውም ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *