መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 17፤2014-በሊቢያ የጋዳፊ ልጅ በፍርድ ቤት ሊያቀርቡት የነበረዉን ይግባኝ ታጣቂዎች ማስቆማቸዉ ተሰማ

በሊቢያ የጋዳፊ ልጅ በፍርድ ቤት ሊያቀርቡት የነበረዉን ይግባኝ ታጣቂዎች ማስቆማቸዉ ተሰማ

የጦር መሳሪያ ያነገቡ ታጣቂዎች የሊቢያ ፍርድ ቤት ዘልቀው በመግባት ዳኞች ሰይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ ከፕሬዚዳንታዊ ውድድር እንዲገለሉ መወሰናቸዉን ተከትሎ የቀረበዉን ይግባኝ እንዳይመለከቱ መከልከላቸዉን የጋዳፊ ልጅ ጠበቃው ተናግረዋል፡፡ጠበቃ ካሊድ ዘይዲ በሊቢያ ሴብሃ ከተማ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ችሎቱ ሊካሄድ ያልቻለው የፍርድ ቤቱ ሰራተኞች እና ዳኞች በጠመንጃ አፈሙዝ በመባረራቸዉ የተነሳ ነዉ ብለዋል፡፡

እርምጃው ተቀባይነት የሌለውና ስልጣኔ የጎደለው ነው ሲሉ የገለጹት ጠበቃዉ በምርጫው ሂደት ላይ አንድምታ ይኖረዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።የምርጫ ኮሚሽኑ ለፕሬዚዳንታዊ ውድድር የሊቢያው ሟቹ መሪ ሙአመር ጋዳፊ ልጅን ጨምሮ የበርካታ አመልካቾችን ዕጩነት ህጋዊ ምክንያቶችን በመጥቀስ ውድቅ አድርጓል።

ሰይፍ አል ኢስላም በአባታቸው አገዛዝ ላይ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመጽ ወቅት በተከሰሱባቸው የጦር ወንጀሎች በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ይፈለጋሉ።የሊቢያ ወታደራዊ አቃቤ ህግ በበኩሉ የጋዳፊ ልጅ እና የጦር አበጋዙ ካሊፋ ሃፍታር ላይ በተመሰረተባቸው የወንጀል ክስ እስኪጠየቁ ድረስ የምርጫ ኮሚሽኑን ስራ እንዲያቆም ጠይቀው ነበር።

በትላንትናዉ እለት፣ ሚስራታ ፍርድ ቤት እ.ኤ.አ በ2019 የሚስራታ ወታደራዊ ኮሌጅን በቦምብ በማፈንዳት እና በብሄራዊ አንድነት መንግስት ላይ ባመፁ የሊቢያ ወታደሮችን በመግደላቸው በሃፍታር ላይ በሌሉበት የሞት ፍርድ አስተላልፏል።ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሃፍታር እጩነት ግን በምርጫ ኮሚሽኑ የተረጋገጠ ይመስላል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *