መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 17፤2014-በደብረ ብርሃን ከተማ የእንቅስቃሴ ገደብ ቢኖርም ድጋፍ ይዘው ለሚመጡ ግን በሩ ክፍት ነው ተባለ

በደብረ ብርሃን ከተማ የእንቅስቃሴ ገደብ ቢኖርም ድጋፍ ይዘው ለሚመጡ ግን በሩ ክፍት ነው ተባለ

የደብረብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ እንደገለጹት የአሸባሪው ቡድን አባላት ከተፋናቃዮች ጋር ተመሳስለው ወደ ከተማው በመግባት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛትም ሆነ በሌሎች መንገዶች የከተማውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዳያውኩ እንዲሁም ለተፈናቃዮችም ሆነ ለከተማው ህዝብ ደህንነት ሲባል ከህዳር 16 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የቀን እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችሉት የደብረብርሃን ከተማ መታወቂያ የያዙ ብቻ መሆን እንዳለባቸው የእንቅስቃሴ ገደብ ለመጣል ከተማ አስተዳደሩ መገደዱን አስታውሰዋል፡፡

የእንቅስቃሴ ገደቡ ዓላማ ሰርጎ ገቦችን ለመቆጣጠር ታሳቢ ያደረገ ነው እንጂ ጤናማ እንቅስቃሴዎችን ለማገድ ታስቦ አለመሆኑን ሁሉም ሰው በውል እንዲረዳው እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡በዚህም በከተማው የእንቅስቃሴ ገደቡ ቢኖርም ለተጎጂዎች ድጋፍ ይዘው ለሚመጡ ግን በሩ ክፍት መሆኑን የደብረ ብርሃን ከተማ ሰላም እና ደህንነት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡

በመሆኑም ከቀያቸው ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን ለሚገኙ ወገኖች ከየትኛውም የሀገሪቱ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ ይዘው መምጣት የሚፈልጉ ሁሉ ክልከላው እንደማይመለከታቸው አውቀው ወደ ከተማው መምጣት እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *