
ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የኢዜማ አባላት በዛሬው እለት ሽኝት ሊደረግላቸው ነው !!
ሀገር የማዳን ተልዕኮ የተቀበሉ የኢትዮጲያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የፖለቲካ ፓርቲ አባላት በዛሬው እለት በፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አማካይነት ሽኝት ሊደረግላቸው እንደሆነ ታውቋል ፡፡
አባላቱ በትላንትናው እለት በከተማ አቀፍ በተደረገው ሽኝት ላይ ተገኝተዋል የተባለ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ እነዚሁ አባላት በፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በኩል በፅ/ቤቱ አማካይነት እንደሚሸኙ የኢዜማ ፖለቲካ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት ወርቅነህ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ፡፡
የሀገርን ጉዳይ ለማንም አሳልፈን የምንሰጠው አይደለም ያሉት ሃላፊዋ ሁሉንም ልዩነቶች ወደ ጎን ትቶ ሀገር የማዳን ስራው ላይ ሁሉም ሊረባረብ ይገባል ብለዋል ፡፡
ሀገር የከፋ ነገር ላይ እንድትደርስ ያደረገው የሽብር ቡድኑ አካሄድ ነው ያሉት የባልደራስ የፖለቲካ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ የፓርቲያቸው አማራሮች እና አባላት ወደ ግንባር ለመሄድ ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል ፡፡
ናትናኤል ሀብታሙ