መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 20፤2014-በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ12 ሺሕ በላይ ዜጎች በኤችአይቪ ኤድስ ህይወታቸው እንደሚነጠቁ ተነገረ

በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ12 ሺሕ በላይ ዜጎች በኤችአይቪ ኤድስ ህይወታቸው እንደሚነጠቁ ተነገረ

የኤችአይቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፅህፈት ቤት ፤ በየአመቱ ከ12 ሺሕ በላይ ዜጎች በኤችአይቪ ኤድስ ህይወታቸውን ሲያጡ ፣ ከ10 ሺሕ በላይ የሚሆኑ አዲስ በቫይረሱ እንደሚያዙ አስታውቋል።

ይኸውም ቀደም ካሉት ጊዜያቶች ጋር ሲነፃፀር አሁን ላይ የሞት ምጣኔው ቀንሷል ቢባልም ፤ ብዙ ዜጎች በኤችአይቪ ኤድስ ህይወታቸውን እየተነጠቁ ይገኛል። 67 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ የሚይዙት ደግሞ ወጣቶች መሆናቸው ተጠቅሷል።

የጽህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል በትረ ፤ ከተጠቀሱት መካከል አብዛኛውን ድርሻ የሚይዙት እድሜያቸው ከ30 አመት በታች የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸውን በተለይ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

በሽታውን ለመከላከል የወጣቶችን ግንዛቤ ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰትቶ መስራት ካልተቻለ ፤ ኢትዮጵያ አምራች ዜጋዋን በከፍተኛ ሁኔታ ልታጣ ትችላለች ሲሉ ስጋታቸውን አስረድተዋል።

በማህበረሰቡ ዘንድ የበሽታውን ስርጭት መቆጣጠር ተችሏል በሚል እሳቤ መዘናጋት መኖሩ ፣ ለቫይረሱ ተጋላጭነት ዋነኛው ምክንያት መሆኑን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ዳንኤል በትረ አስረድተዋል።

የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እንደ ከዚህ ቀደሙ አለመሆኑም ወጣቱ ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ ማድረጉ ሌላው ተጠቃሽ ነው። ችግሩንም ለመቅረፍ ከግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ባሻገር ፤ የሚመለካቸው አካላት ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች ይከናወናል ተብሏል።

ቅድስት ደጀኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *