መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 20፤2014-በጭፍራ አሸባሪዉ ህወሓት በሀይማኖት ተቋማት ላይ ጉዳት ማድረሱን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አረጋገጠ

በአፋር ክልል በጭፍራ አሸባሪዉ ህወሓት የሀይማኖት ተቋማትን ማዉደሙን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ሰላማዊት ካሳ አስታዉቀዋል ።

በመከላከያ ሰራዊታችን በቅርቡ በቁጥጥር ስር በሆነችዉ ጭፍራ ህወሓት በመስጊዶችን ላይ ጥቃት ማድረሱን እና ቅዱሳን መጽሀፍትን ማዉደሙን ሚኒስትር ድኤታዋ ገልጸዋል።

ሚኒስትር ድኤታዋ በማብራራርያቸዉ
በሰራዊቱ የሚደርስበትን ጥቃት በመሸሽ ላይ የሚገኘውን አሸባሪ በንብረት እና በአካባቢዉ ሰላም ላይ የሚያደርሰዉን ጥፋት ለመከላከል ህብረተሰቡ ተደራጅቶ አካባቢዉን መጠበቅ እንዳለበትም አሳስበዋል።

በተጨማሪም ሚኒስቴር ድኤታዋ በመግለጫቸዉ መንግሥት ሀገራዊ ፋይዳቸዉ ከፍ ያሉ ፕሮጀክቶችን ቅድሚያ በመስጠት የበጀት ሽግግሽግ በማድረግ አፈጻጸማቸዉን ላይ ጠንካራ ክትትልን እያደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

በረከት ሞገስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *