
ታይዋን እና አውሮጳ ዲሞክራሲን ለመጠበቅ በጋራ መስራት አለባቸው ሲሉ የታይዋን ፕሬዝዳንት ተናገሩ
ታይዋን እና አውሮጳ አምባገነንነትን እና የተዛባ መረጃን ለመከላከል በጋራ መስራት እንዳለባቸው የታይዋን ፕሬዝዳንት ጻ ኢንግ-ዌን ከባልቲክ ሀገራቱ ሊትዌኒያ፣ ላትቪያ እና ከኢስቶኒያ ከመጡ የምክር ቤት አባላት ጋር ከመከሩ በኃላ በዛሬው እለት ተናግረዋል።ሊትዌኒያ የታይዋን ኤምባሲ በሀገሯ እንድትከፍት መፍቀዷን ተከትሎ ድርጊቷ ቻይናን አስቆጥቷል።
ቻይና ታይዋንን የራሴ ግዛት ናት የምትል ሲሆን የሊትዌኒያ ውሳኔን ተከትሎ ቻይና ከፍተኛ ተፅእኖ እያደረገችባት ትገኛለች።ታይዋን ዓለም አቀፋዊ ተሳትፎን በመገደብ የቻይናን ሉዐላዊነት እንድትቀበል ቤጂንግ የወታደራዊ እና የዲፕሎማሲ ጫና በታይፔ ላይ ማድረጓን ቀጥላለች።
ታይዋን ምንም እንኳን ጫናው ቢበረታም ነፃነቷን እና ዲሞክራሲዋን እንደምትጠብቅ ትናገራለች።በአንድ ወቅት የሶቭየት ህብረት አካል የነበሩት የባልቲክ ሀገራይ ለነፃነታቸው ሲታገሉ ተመሳሳይ ተሞክሮን እንጋራለን ሲሉ ጻ ኢንግ-ዌን ተናግረዋል።
በሚኪያስ ፀጋዬ