መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 21፤2014-ባርባዶስ ከንግሥት ኤልዛቤት 2ኛ ርዕሰ መስተዳድር በይፋ ራሷን በማላቀቅ የዓለም አዲሲቷ የሪፐብሊክ ሀገር ሆነች

ባርባዶስ ከንግሥት ኤልዛቤት 2ኛ ርዕሰ መስተዳድር በይፋ ራሷን በማላቀቅ የዓለም አዲሲቷ የሪፐብሊክ ሀገር ሆነች

በዋና ከተማይቱ ብሪጅታውን በተካሄደ ሥነ ሥርዓት፣ ዴም ሳንድራ ሜሰን የባርባዶስ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡የዌልሱ ልኡል እና የባርባዶስ ዜግነት ያላት ድምጻዊቷ ሪሃና ነመድረኩ በመገኘት የሀገሪቱን 55ኛ የነጻነት በአል ላይ አክብረዋል፡፡

ልዑል ቻርለስ ባደረጉት ንግግር የካሪቢያን የደሴት ሀገር የሆነችዉ ባርባዶስ የደረሰባትን አሳዛኝ የባርነት አረመኔያዊ ድርጊት በይፋ እዉቅና ሰጥተዋል፡፡ደሴቲቱ በአትላንቲክ የባሪያ ንግድ ዋና ማዕከል የነበረችበትን ከ200 የሚበልጡ ዓመታት ጨምሮ የብሪታንያ የዘመናት ተጽዕኖ ማብቃቱ ይፋ ሆኗል፡፡

ይፋዊ የስልጣን ለውጥ ለማመልከት የብሪቲሽ ንጉሳዊ አገዛዝ የመጨረሻ ስንብት በማድረግ የሮያል ስታንዳርድ ሰንደቅ እንዲወርድ ተደርጓል፡፡በዝግጅቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ልዑል ቻርልስ በህገ መንግስታዊ ደረጃ ቢቀየርም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ንግስቲቱ ለቀጣይ ሰላም፣ ደስታ ፣ እና ብልጽግና ያላቸዉን መልካም ምኞት በመላክ የባርባዶስ ህዝብ በልቧ ውስጥ ልዩ ቦታ እንዳለዉ ተናግራለች።

እ.ኤ.አ. ከ2018 ጀምሮ የደሴቲቱ ዋና ገዥ የነበሩት የ72 ዓመቷ ዴም ሳንድራ ሜሰን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ባለፈው ወር የተመረጡ ሲሆን አሁን ላይ የንግስቲቱን የርዕሰ መስተዳድርነት ቦታ ያስቀራል፡፡ የሽግግሩ ደጋፊዎች ከባርባዶስ ርዕሰ መስተዳድርነት የብሪታንያ ንግስት መወገዷ ከፍተኛ መልዕክት ያስተላልፋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *