መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 21፤2014-የበሻሸመኔ ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት 560 ኪ.ግ የሀሺሽ እፅ በቁጥጥር ስር ዋለ

በሻሸመኔ ከተማ መስተዳር በተደረገ ቁጥጥር እና ፍተሻ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በድብቅ የተገኘ የኮንትሮባድ እቃ እና የሀሺሽ በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማው ፖሊስ አስታዉቋል፡፡

የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ የወረዳ 2 ፖሊስ ፅ/ቤት የምርመራ እና ፍትህ የመስጠት የስራ ሂደት ባለቤት ኢንስፔክተር ደሳለኝ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት በሻሸመኔ ከተማ ወረዳ 2 በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ 23 ቦንዳ ልባሽ ጨርቆች እና 560 ኪሎ ግራም የሀሺሽ እፅ መያዙን ተናግረዋል፡፡

የቦንዳ ልብስ እና የሀሺሽ እፅ የተገኘው ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት በሰጠው ጥቆማ መሰረት መሆኑን ኢንስፔክተር ደሳለኝ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *