መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 21፤2014-የትዊተር መስራች ጃክ ዶርሲ ከዋና ስራ አስፈፃሚነቱ ለቀቀ

የትዊተር መስራች ጃክ ዶርሲ ከዋና ስራ አስፈፃሚነቱ ለቀቀ

የትዊተር መስራች ጃክ ዶርሲ ከኩባንያውን ዋና ስራ አስፈፃሚነት ቦታ መልቀቁ ተሰምቷል፡፡ ጃክ ዶርሲ ከስልጣኑ መልቀቁን ተከትሎ የትዊተር ዋና ቴክኒካል ኃላፊ ፓራግ አግራዋል በቦታው ይተካዋል ሲል ትዊተር አስታዉቋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2006 ትዊተርን የመሰረተው ዶርሲ የትዊተር እና የክፍያ ድርጅት የሆነው ስኩዌር ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን እያገለገለ ይገኛል።

ኩባንያው ለመልቀቅ ዝግጁ ነኝ በማለት በመጨረሻ የምሄድበት ጊዜው አሁን ነው ሲል ጃክ ዶርሲ በትዊተር ላይ ጽፏል።ዶርሲ ስልጣኑን በሚረከበው ፓራግ አግራዋል ላይ ጥልቅ እምነት አለኝ ሲል ተናግሯል።ለችሎታው፣ለማንነቱ አመስጋኝ ነኝ ኩባንያውን ለመምራት አሁን ጊዜው የእርሱ ነው ሲል ጃክ ዶርሲ ተናግሯል።

አግራዋል ትዊተርን የተቀላቀለው እ.ኤ.አ. በ2011 ሲሆን ከ2017 ጀምሮ የኩባንያው የቴክኖሎጂ ኃላፊ ሆኖ አገልግሏል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *