መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 22፤2014-ኢልሃን ኦማር የግድያ ዛቻ እንደደረሰባት አስታወቀች

ዲሞክራቷ የሚኒሶታ ተወካይ ኢልሃን ኦማር በድምጽ መልእክት አሰቃቂ የግድያ ዛቻ እንደተላከላት አስታዉቃለች ፣የምክር ቤቱ የሪፐብሊካኑ መሪዎች በየደረጃቸው ያለውን ጥላቻ መሰረት ያደረገ ማስፈራሪያን ለመቅረፍ እና ይህንን የሚያራምዱትን በህግ እንዲጠየቁ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ከሙስሊም የኮንግረስ አባላት መካከል አንዷ የሆነችው ኢልሃን ኦማር በኮንግረሱ ውስጥ በወግ አጥባቂ አባላት እና አንዳንድ ሪፐብሊካኖች ዘንድ በተደጋጋሚ ጥቃት ሲሰነዘርባት ቆይቷል፡፡በዚህም የተነሳ የሚደርሳት ጥቃት ወደ ግድያ ዛቻ እንዲጨምር አድርጓል።

በቅርቡ የኮሎራዶ ተወካይ የሆነችዉ ላውረን ቦበርት ኢልሃን ኦማርን “የሽብር ጓድ” አባል በማለት ቦምብ ከተሸከመ አሸባሪ ጋር የሚያመሳስል ቪዲዮ ለቃለች፡፡ቦበርት ከዚህ ድርጊቷ በኃላ ኢልሃን ኦማርን ይቅርታ መጠየቋ ይታወሳል፡፡

ከ2019 ጀምሮ በሚኒሶታ 5ኛ ኮንግረስ አውራጃ ተወካይ ሆኖ በማገልገል ላይ የምትገኘዉ የሶማሊያ ተወላጅ አሜሪካዊቷ ፖለቲከኛ ተጽእኖ ፈጣሪ ለመሆን በቅታለች፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *