መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 22፤2014-የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ሲገለገልበት የነበረውን የንግድ ምልክት እና ስያሜ ሊቀይር ነው❗️

በፋይናንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ ከሚገኙ 16 የግል ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ፣ መለያ አርማውን በአዲስ ሊቀይር መሆኑን አስታውቋል

ለ13 ዓመታት ያገለገለውን የልዩ ምልክት ዓርማ በአዲስ ለመቀየር የታሰበው ያለፉትን ዓመታት ውጤታማ የነበረ የስራ ጊዜ እንዲሁም የወደፊቱን ብሩህ ተስፋና ዛሬ የደረስንበትን ጽኑ መሠረት እንዲገልጽ እንዲሁም የመጪውን ስሜትና ለውጥ ያማከል መሆኑን የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ተፈሪ መኮንን ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል፡፡

አዲሱ የባንኩ መግለጫ ዓርማ ለደንበኞችና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት የባንኩ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች፣ ያለፈውን ስኬትና የወደፊቱን ግብ በሚወክል ከሌሎች ተወዳዳሪዎች በቀላሉ ለይተው እንዲያውቁትና እንዲያስታውሱት በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል ፡፡

አያይዘውም የባንኩን ገጽታም በወጥነት ለማስተዋወቅና ትኩረትን በመሳብ ባንኩን ለማስተዋወቅ የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ እና ወደ ፊት ከዚህ በበለጠ መልኩ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሞላት እንደሚሰራ ፕሬዚዳንቱ አቶ ተፈሪ መኮነን ለብስራት ራዲዮ ገልጸዋል ፡፡

በኤደን ሽመልስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *