
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ”የ1 ሚሊየን ወደ አገር ቤት” ዘመቻ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት ጥሪ የአውሮፓውያኑን አዲስ ዓመት በኢትዮጵያ ለማክበር ይፋ የሆነውን 1 ሚሊየን ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የማድረግ ጥሪን እንዲቀበሉ ጠይቀዋል፡፡