
አሸባሪዉ ህወሓት በአማራ ክልል የላሊበላ ዉቅር አብያተ ክርሲቲያን የሚገኝበት ስፍራን ጨምሮ በስድስት የሀይማኖት ተቋማት ላይ ዉድመት ማድረሱን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት ካሳ ተናግረዋል ።
ህወሓት በወረራ ይዟቸዉ በቆዩ ቦታዎች በአንጾኪያ እና በጋሸና ንጹሀን ዜጎችን በጅምላ መጨፍጨፉን እና በአፋር እና በአማራ ክልሎች የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደፈጸመ ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በ አማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን ህወሓት ወድቶችን ማስከተሉን ሚኒስትር ድኤታዋ በመግለጫቸዉ አስታውቀዋል። በዚህም እስካሁን በተደረገው ጥናት ሁለት የባህልና ቱሪዝም ተቋማት እና 22 የቱሪዝም አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል ። አያይዘውም አሸባሪዉ ህወሓት በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ሊገኝ የሚችለዉን 7.1ሚሊዮን ብር ገቢ ማሳጣቱን ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት በሰጡት መግለጫ ላይ አንስተዋል።