መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 27፤2014-ኢራን የኒውክሌር ጥሰት በመፈፀሟ ዋጋ መክፈል አለባት ስትል እስራኤል ተናገረች

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት የአለም ኃያላን ሀገራት ዓለም አቀፍ የኒውክሌር ስምምነት ላይ ለመድረስ በሚደረገው ድርድር ላይ ጠንካራ አቋም እንዲይዙ አሳስበዋል።የእስራኤል ከፍተኛ የስለላ እና የመከላከያ ባለስልጣናት ወደ ዋሽንግተን በዚሁ ዙሪያ ውይይት ለማድረግ ባቀኑበት ወቅት ጠ/ሚ ቤኔት ይህንኑ አስተያየት ሰጥተዋል።

እ.ኤ.አ በ2015 የተፈረመውን ስምምነት ወደ ቀድሞ ሁኔታ ለመመለስ የዓለም ኃያላን ሀገራት ከኢራን ጋር በቪየና ለውይይት ሲቀመጡ እስራኤሉ ጉዳዩን በጭንቀት ስትከታተል ቆይታለች።ኢራን ንግግሮች እንደገና እንዲቀጥሉ መደራደር እንደሚቻል ጠቁማለች።

ቤኔት በትላንትናው እለት ለሀገሪቱ ካቢኔው እንደተናገሩት በቪየና ከኢራን ጋር የሚደራደሩ ሁሉም ሀገራት ጠንካራ አቋም እንዲይዙና ዩራንየምን ማበልፀግ እና መደራደር እንደማይችሉ ለኢራን ግልፅ እንዲያደርጉ እጠይቃለሁ ብለዋል።ኢራን ለፈፀመችው ጥሰት ዋጋ መክፈል መጀመር አለባት ስትል እስራኤል ተደምጣለች።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *