መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 27፤2014-የምያንማር ፍርድ ቤት ከስልጣን የተባረሩትን የቀድሞ የሀገሪቱ መሪ የአራት አመት እስራት ፈረደባቸዉ

ከስልጣን የተባረሩት የምያንማር የቀድሞ መሪዋ አንግ ሳን ሱ ኪ የአራት አመት እስራት ተፈርዶባቸዋል፤ እስከ እድሜ ልክ ሊያስቀጣቸዉ ከሚችለዉ ክስ ዉስጥ የመጀመሪያዉ ዉሳኔ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ተቃውሞን በማነሳሳት እና የኮቪድ ህጎችን በመጣስ ጥፋተኛ ሲል ፍርድ ቤቱ ዉሳኔዉን አሳልፏል፡፡

ሳን ሱ ሱ ኪ በአጠቃላይ 11 ክሶች የቀረበባቸዉ ሲሆን የቀረቡባቸዉ ክሶች ፍትሃዊ አይደሉም በሚል በሰፊው እየተወገዙ ይረገኛል፡፡ሳንሱ ኪ የቀረበባቸዉን ሁሉንም ክሶች የሀሰት ሲሉ ዉድቅ ያደርጋሉ፡፡ባለፈዉ ዓመት የካቲት ወር በተካሄደዉ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተወገዱት አንግ ሳን ሱ ኪ ለወራት የቁም እስረኛ ነበሩ፡፡ ሱ ኪ ወደ እስር ቤት የሚገቡት መቼ እንደሆነ በግልፅ የተነገረ የለም፡፡

በተመሳሳይ ክስ የምያንማር የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዊን ሚይንት እና ብሄራዊ ሊግ ለዲሞክራሲ የቀድሞ ገዢዉ ፓርቲ አጋር መሪ የሱ ኪ በዚሁ ክስ እያንዳንዳቸዉ በአራት አመታት እስር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ሰኞ ዉሳኔ አሳልፏል፡፡

የመብት ተሟጋች ድርጅት የሆነዉ አምነስቲ ክሱን ሀሰት ሲል ወታደራዊ አስተዳደር ተቃዋሚዎቹን በሙሉ ለማስወገድ እና በምያንማር ውስጥ ነፃነቶችን ለማፈን የወሰደውን እርምጃ የመጨረሻው ምሳሌ ነው ሲል ገልጾታል፡፡የ76 አመቷ አዛውንት አንግ ሳን ሱ ኪ በተለያዩ የሙስና ክሶች እና ይፋዊ ሚስጥሮችን በመጣስ ወንጀሎች ክስ ተከፍቶባቸዉ ይገኛል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *