መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 29፤2014-በሞዛምቢክ የሚገኙ ታጣቂዎች ቢያንስ 600 ሴቶችን ማገታቸው ተሰማ

በሞዛምቢክ ሰሜናዊ የካቦ ዴልጋዶ ግዛት ቢያንስ 600 ሴቶች እና ልጃገረዶች ባለፉት ሶስት ዓመታት በታጣቂዎች ታግተው ለባርነት መዳረጋቸውን ሂዩማን ራይትስ ዎች ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል።

ከእገታው ጀርባ ከአይኤስ ጋር በቅንጅት ይሰራሉ የተባሉት የአልሻባብ ቡድን ታጣቂዎች እጃቸው እንዳለበት ተነግሯል።በሪፖርቱ የቆዳቸው ቀለም ቀላ ያሉ ሴቶችና ልጃገረዶችን ላይ እገታ በመፈፀም የታጣቂው ቡድን አባላት በግዳጅ በትዳር እንዲጣመሩ ተደርገዋል።

እገታ ከተፈፀመባቸው መካከል አንዳንዶቹ ከ600 እስከ 1800 ዶላር ለውጪ ሀገር ታጣቂዎች እንዲሸጡ ተደርጓል።በቤተሰቦቻቸው አማካይነት ገንዘብ የተከፈለላቸው ሴቶች ከታጣቂዎቹ መዳፍ መውጣት ችለዋል።

በመንግስት ሀይሎች እና በታጣቂ ቡድኑ መካከል በተደረገ ውጊያ ማምለጥ የቻሉ ሴቶችም አሉ።በታጣቂዎች ታግተው የሚገኙ ሴቶች እንዲለቀቁ ሂዩማን ራይክስ ዎች ጥሪ አቅርቧል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *