መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 29፤2014-ኦላፍ ሾልስ አዲሱ የጀርመን ቻንስለር በመሆን ቃለ መኃላ ፈፀሙ፤የሜርኬል የ16 ዓመታት አመራር ተጠናቋል❗️

ኦላፍ ሾልስ የጀርመን አዲሱ ቻንስለር በመሆን ቃለ መሃላ ፈፅመዋል፤ ይህም የአንጌላ ሜርክልን የ16 አመታት ታሪካዊ የመሪነነት ዘመን ፍጻሜ ሆኗል። የሶስትዮሽ ፓርቲ ጥምረት በጀርመን ፓርላማ አብላጫ ድምጽ በማግኘት ስልጣናቸውን ተረክበዋል።

የመሀል ግራው ሶሻል ዴሞክራት ፓርቲያቸው ከአረንጓዴዎቹ እና ለንግድ ስራ ተስማሚ ከሚባሉት የፍሪ ዴሞክራቶች ጋር በመሆን ያስተዳድራል። የስልጣን ርክክቡ የወይዘሮ ሜርክል የ31 አመታት የፖለቲካ ህይወት ማብቂያ ይሆናል።

የ63 አመቱ ሾልዝ ምክትል ቻንስለር በመሆን በሜርክል መንግስት ውስጥ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። የጀርመን ፓርላማ ቡንደስታጉ ሹመቱን በ 395 ድምፅ ድጋፍና በ303 ድምጽ ተቃውሞ አፅድቋል።የጀርመን ፕሬዚዳንት ፍራንክ ዋልተር ሽታይንማየር ዘጠነኛው የፌደራል ቻንስለር በመሆን ሾልዝ በይፋ መሾማቸውን አውጀዋል።

አዲሱ መንግስት የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ትልቅ ዕቅዶች እንዳሉት ያስታወቀ ሲሆን የድንጋይ ከሰል በማስቆም እና በታዳሽ ሃይል ላይ በማተኮር እንደሚሰራ ተልጿል። የመንግስታቸው የቅድሚያ ተግባር ግን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መዋጋት መሆኑ ተመልክቷል።የጀርመን የጤና ባለሥልጣናት ባለፉት 24 ሰዓታት 527 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን አጥተዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *