
መከላከልን መሰረት አድርጎ እየተሰራ የሚገኘው የጤና አገልግሎት ለውጥ ማምጣቱን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ።ይሁን እንጂ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ፍትሃዊነት ባለው መልኩ ማዳረስ በሚገባው ልክ እየተዳረስ እንዳልሆነ ተነግሯል ።
ለዚህ ቀዳሚው ምክንያት የመንግስት እና የዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎች ክፍያ ሳይከለስ መቆየቱ ክፍተት ፍጥሯል ሲሉ የጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና የኮሚዩኒኬሽን ሃላፊው ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ።
በእዚህ መነሻነትም የመንግስት የጤና ተቋማት ከመንግስት ከሚመደብላቸው በጀት እራሳቸውን እንዲያጠናክሩ መመሪያው ቢፈቅድም ያለፉትን አርባ ዓመታት የክፍያ ስርዓቱ ሳይከለስ መቆየቱ የፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት ሲባ የክፍያ ስርዓቱ መከለስ እንዳስፈለገው በጤና ሚኒስቴር የአጋርነት እና ትብብር ዳይሬክተር ዶ/ር ፌቨን ግርማ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ።
ይህ የክፍያ ክለሳው የህብረተሰቡን አቅም ያገናዘበ ይሆናል ያሉት ዳይሬክተሯ አቅሙ ለሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ይሰጥ የነበረው እስከ ነፃ የሚደርሰው አገልግሎት ሂደት እንደሚቀጥል በተጨማሪነት ተነስቷል።
በዚህ ሂደትም በመደበኛው የኢኮኖሚ ዘርፍ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በራሳቸው ላይ የተጠቀሰውን 45 በመቶ ወጪ የሚሸፍኑ ይሆናል ተብሏል ።
ናትናኤል ሀብታሙ