መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 30፣2014-በህዳር ወር ብቻ ከ15ሺ በላይ ከረጢት ደም ተሰበሰበ❗️

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አሸባሪው ተብሎ የተፈረጀው የህውሃት ቡድን የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች ጉዳቶች መከሰታቸው ይታወቃል።

ይህንኑ ተከትሎ የብሄራዊ ደም ባንክ የደም እጥረት እንዳያጋጥም አስቀድሞ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ደሜን ለመከላከያ ሰራዊት በሚል መሪ ቃል የደም ማሰባሰብ መርሀ ግብር ማዘጋጀቱ አይዘነጋም።

በዛሬው እለት በሚጠናቀቀው በህዳር ወር 15 ሺ 286 ከረጢት ደም መሰብሰቡን በብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት የደም ለጋሾች ዘርፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ተመስገን አበጀ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ እና በክልሎች በቂ እና ከበቂ በላይ የሚባል የደም ክምችት መኖሩም ተገልጿል። ከጦርነት ቀጠና ውጪ የሆኑት ደም ባንኮች እየሰሩ እንደሚገኝ እና ለተጎጂዎች ተደራሽ ይደረጋል።

ከሚሴ፣ወልዲያ እና ደሴ የደም ባንኮች እንደማይሰሩ እና በንብረት ላይ ጉዳት የደረሰባቸው እና በቀጣይም ባንኮቹን የማቆቆም ስራ እንደሚሰራ ዶ/ር ተመስገን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *