
ታሪካዊቷ የደሴ ከተማ በጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ከአሸባሪዉ የህውኃት ቡድን ነጻ ከወጣችበት ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የወደሙ ንብረቶችን የማጣራት እና ከተማዋን የማረጋጋት ስራ እየተሰራ መሆኑን የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል ተናግረዋል፡፡ከንቲባው አቶ አበበ ከብስራት ሬድዮ ጋር በነበራቸው የስልክ ቆይታ ከተማዋ በአሁኑ ወቅት ሰላማዊ መሆናን ያነሱ ሲሆን በአሸባሪው ህውሀት በርካታ የመንግስት ንብረቶች መውደማቸውን ገልጸዋል፡፡
የደሴ ከተማን ሰላም የማረጋጋት የጸጥታ ስራ እንዲሁም በከተማዋ ላይ የወደሙ ንብረቶችን የመለየት እና መልሶ የማቋቋም ስራ ከሚመለከታው አካላት ጋር እየተወያዩ መሆኑን አንስተዋል፡፡በቀጣም ስለወደሙት ንብረትም ሆነ ስለደረሱ ጉዳቶች ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡
ደሴ ለንግድ እንቅስቃሴ መተላለፊያ ዋና ኮሪደር እና ለወደብ ቅርብ ከተማ ናት፡፡የደሴ ከተማ በጢጣ በር በኩል ወደ ትግራይ ፣በቢለን ወይም ገራዶ በኩል ደግሞ ወደ ሸዋ እና ጐጃም ፣ በኩታበር በኩል ወደ ጎንደር ፣ በቁርቁር በር በኩል ወደ ላስታ እና ወደ ሌሎችም አካባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግባት በአማራ ክልላዊ መንግስት ስር የምትገኝ ታሪካዊ ከተማ ናት
የደሴ ከተማ ከአዲስ አበባ በሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ በ400 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡
ትግስት ላቀዉ