በደብረማርቆስ ከተማ ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ሰፈር 4 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እታገኝ ተካ የተባለች ግለሰብ የአስችኳይ ጊዜ አዋጁን በመተላለፍ እንዲሁም የኮቪድ 19 መመሪያዎች በመጣስ ህዳር ሰባት ቀን ከቀኑ አስር ሰአት ላይ አስራ አንድ የሚሆኑ ሰዎች በመኖሪያ ቤቷ በማሰባሰብ ሺሻ ስታስጨስ በቁጥጥር ስር ውላለች ።
በመሆኑም ፖሊስ ጉዳዩን ሲመረምር ቆይቶ የደብረ ማርቆስ ከተማ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የሁለት አመት እስራት እንዲሁም የሁለት ሺህ ብር ቅጣት እንደተላለፈባት የደብረማርቆስ ከተማ ፖሊስ የወንጀል መርማሪ የሆኑት ምክትል ኮማንደር አበበች አምሳሉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።
አያያዘውም እንደገልጹት ከሆነ ህብረተሰቡ ህግን ተላልፎ ያልተገባ ተግባር የሚፈጽም አካላትን እንዲሁም ሌሎች አጠራጣሪ ነገሮች ከተመለከተ 058 771 1232 በመደወል ጥቆማ እንዲያድርጉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በኤደን ሽመልስ