መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 30፣2014-የመከላከያ ዋና ጄኔራል እና ሚስቱን ጨምሮ 11 ሰዎች በሄሌኮፍተር መከስከስ አደጋ ህይወታቸዉ አለፈ❗️

የህንድ የመከላከያ ኃላፊ ጄነራል ቢፒን ራዋት እና ባለቤታቸዉን ጨምሮ ሌሎች 11 ሰዎች በታሚል ናዱ የጦሩ ሄሌኮፍተር መከስከስ አደጋ ህይወታቸዉን እንዳጡ የህንድ አየር ሀይል አስታወቁ፡፡የህንድ አየር ሀይል በትዊተር ገፁ ላይ አሳዛኝ አደጋ ሲል የገለጸ ሲሆን አደጋዉ በትላንትናዉ እለት እኩለ ቀን ኮኖር ከተማ አቅራቢያ ደርሷል፡፡

ሩሲያ ሰራሽ የሆነችው ማይ-17 ቪ 5 ሄሊኮፕተር ከአየር ሃይል ወደ መከላከያ አገልግሎት ስታፍ ኮሌጅ በመጓዝ ላይ እያለ አደጋዉ ደርሷለ፡፡የአደጋው መንስኤ ለጊዜው ያልታወቀ ሲሆን ባለስልጣናቱ ምርመራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።አየር ሃይሉ እንዳስታወቀዉ የቡድን ካፒቴን ቫሩን ሲንግ በህይወት ተርፎ በወታደራዊ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገለት ይገኛል ብሏል።

በህንድ የዜና ማሰራጫዎች ላይ የተላለፉ ቪዲዮዎች ሄሊኮፕተሩ በኮሌጁ አቅራቢያ በሚገኝ ጥቅጥቅ ያለ ደን በተሸፈነዉ አካባቢ በእሳት ነበልባል ውስጥ እንዳለ የሚያሳዩ የአካባቢው ሰዎች እሳቱን ለማጥፋት እና ሬሳ ከፍርስራሹ ውስጥ ለማውጣት ሲሞክሩ ለማዉጣት ታይተዋል፡፡

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሀገሪቱን የጦር ኃይሎች እና የፀጥታ አካላትን ለማዘመን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደረጉ “ታላቅ ወታደር” እና “እውነተኛ አርበኛ” ነበሩ ሲሉ ሟቹን ጄኔራል ራዋትን ገልፀዋል። ህልፈቱ በጣም አሳዝኖኛል ሲሉ ሞዲ ተናግሯል። የፓኪስታን ጦር አዛዥ ጄኔራል ካማር ጃቬድ ባጅዋ በራዋት እና በባለቤቱ አሳዛኝ ሞት ሀዘናቸውን ገልፀዋል ሲል መንግስቱ በትዊተር ገፁ አስፍሯል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *