መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 30፣2014-14 የግል የመገናኛ ብዙሃን ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ 2.5 ሚሊን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

በኢትዮጵያ የግል ብሮድካስተሮች ዘርፍ ማህበር አስተባባሪነት በሀገሪቱ ከሚገኙ 14 የግል ንግድ ሚዲያ ተቋማት ‹‹እኔም ለወገኔ›› በሚል ከአፋር እና ከአማራ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ2.5 ሚሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ ከብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራራ ኮሚሽን ጋር በመተባባር በክልሎቹ በሚገኙ እርዳታ ማእከላት እና መጠለያ ካምፖች ያለውን አሰቸኳይ ፍላጎት መሰረት ያደረገ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ድጋፉ 250 ኩንታል ስንዴ ዱቄት፣ 1000 ብርድልብስ፣ 400 ፍራሽ ፣7200 ህጻናትን ለአንድ ሳምንት መመገብ የሚችል 300 ካርቶን አልሚ ምግብ በኮሚሽኑ በኩል ለሁለቱም ክልሎች ተፈናቅለው ለሚገኙ ወገኖች እንዲደርስ ማስረከባቸውን የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር እንደሻው ወ/ሚካኤል በርክከቡ ወቅት ተናግረዋል፡፡

ተቋማቱ በጥምረት እና በተናጠል የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን እንዲሁም ደግሞ የአየር ሰአት በመመደብ አስተዋጾ አድርገዋል፡፡የሚዲያ አካላት በዚህ ሃሳብ ላይ ምንም ዓይነት ድርድር ሳያደርጉ ለወገን መድረስ አለብን ያለንን እናዋጣለን ብለው ይህንን ገንዘብ እንድናሰባስብ ሆኗል ሲሉ የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ እና የዘርፍ ማህበሩ ስራ አስፈጻሚ አቶ አማን ፍስሃ ጺሆን ሲሆኑ የተፈናቀሉት ወገኖች ወደ ቀደመ ነገራቸው እስኪመለሱ ድረስ የሚዲያው አስተዋጽኦ ቀላል ስለማይሆን የተዋቀረው ኮሚቴ ስራወን አያቆምም ብለዋል ፡፡

በቀጣይ እነዚሁ ሚዲያዎች 22.5 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የአየር ሰአት ድጋፍ እንደሚደረግ አቶ አማን ጨምረው ተናግረዋል ፡፡ተቋማቱ ብስራት ሬድዮ፣ ፋና፣ኢቢኤስ፣ኦቢኤስ፣ናሁ፣ አሃዱ፣ዋልታ፣ ቃና፣አርትስ፣ፕራይም፣ኢትዮ፣ዲኤስቲቪ፣ ካናል ፕለስ እና ሀገሬ ናቸዉ፡፡

ቤተልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *