መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 1፤2014-የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የደሴ ማህበረ ምዕመናን በሕወሓት ተዘረፈ!

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ማዕከላዊ ሰሜን ኢትዮጵያ ሲኖዶስ የደሴ ማህበረ ምዕመናን በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ተዘርፏል።
የደሴ መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ቄስ መላኩ ስዩም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ የቤተ ክርስቲያኗ ጥበቃዎችና አገልጋዮች ቁልፍ ካላመጣችሁ ተብለው ተደብድበው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ንብረቶች በአሸባሪው ሕወሓት መዘረፋቸውን ገልጸዋል።

ቄስ መላኩ፤ አሸባሪዎቹ በብዛት የነበሩና ብዙ ብር ወጪ የተደረገባቸውን የድምጽ ማስተካከያና ማቀነባበሪያ መሣሪያዎችን፣ ላፕቶፖችን፣ የፎቶ ካሜራ፣ ኮምፒዩተሮችንና ሌሎች መገልገያ መሣሪያዎች መዘረፋቸውን ገልጸዋል። ይህን ያደረጉት ደግሞ በርና መስኮቶችን በመስበር እንደሆነ ጠቅሰዋል።የአገልጋዮችን መታወቂያ በመቀበልና ፎቶ በማንሳት ያደረጉትን ድርጊት ለየትኛውም አካል ማሳወቅ እንደሌለባቸው አስጠንቅቀዋቸው እንደነበርም አንስተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *