መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 2፤2014-በአሜሪካ ኬንታኪ በከባድና አስከፊ አውሎ ንፋስ ከ70 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

የዩናይትድ ስቴትስ የኬንታኪ ግዛት አስተዳዳሪ ከትላንትና ምሽት አንስቶ በከባድ አውሎ ንፋስ ከ70 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል። የኬንታኪ ገዢ አንዲ በሼር በግዛቲቱ ታሪክ ውስጥ እጅግ የከፋ አውሎ ንፋስ በማለት የሟቾች ቁጥር ከ100 በላይ ሊደርስ ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።

በሜይፊልድ ከተማ የሻማ ፋብሪካ ውስጥ በርካታ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ስጋት ፈጥሯል። በኢሊኖይ የሚገኘውን የአማዞን መጋዘንን ጨምሮ በሌሎች ግዛቶች አውሎ ነፋሱ ከፍተኛ ውድመት በማድረስ ቢያንስ አምስት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

ቤሼር በኬንታኪ ግዛት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ይፋ አድርገዋል። አውሎ ነፋሱ በግዛቲቱ ከዚህ ቀደም ከተከሰቱት ሁሉ እጅግ የከፋው ነው ሲሉም ገልፀዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስለ አውሎ ነፋሱ ገለፃ እንደተደረገላቸው በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። በዚህ አይነት አውሎ ነፋስ የሚወዱትን ሰው ማጣት የማይታሰብ አሳዛኝ ክስተት ነው ሲሉ ገልፀዋል ብሏል። የነፍስ አድን ፍለጋው እና የጉዳት ግምገማ በሚቀጥልበት ጊዜ ከግዛት ገዥዎች ጋር የሚያስፈልጋቸውን እንዲኖራቸው እየሰራን ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *