መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 5፤2014-ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን በህወሓት የሽብር ቡድን የደረሰውን ውድመት ለማሳወቅ ፍቃደኞች አይደሉም ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ

በሽብርተኛው የህወሓት ቡድን የደረሰውን ውድመት ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ለማሳወቅ ፍቃደኞች አይደሉም ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ። አንዳንድ ሀገራት እስከ ዛሬ ድረስ ዜጎቻቸው ከኢትዮጲያ እንዲወጡ መጥራት አለማቆማቸው እንዳለ ሆኖ የሽብርተኛውን ቡድን ጥፋት ምንም አይነት ዘገባ አላወጡም ብለዋል።

አሁንም የኢትዮጲያ መንግስት ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ውድመቱን አይተው እንዲዘግቡ መንገዶችን እናመቻቻለን ሲሊ አምባሳደር ዲና በዛሬው እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን እና ሀገራት በኩል ኢትዮጵያ ላይ የሚደርሰው ጫና እንደቀጠለ ነው ያሉት አምባሳደሩ ይሄ ሁሉ ጥፋት መጥፋቱን ከመዘገብ ይልቅ አሁንም ጫና ማድረግ ላይ ጠንክረው ቀጥለዋል ይሄ ደግሞ የሚያሳዝን ተግባር ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በአውሮፓ ህብረት ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ስለ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉዳይ ለመወያየት ስብሰባ በነገው እለት መጥራታቸውን አስታውሰዋል። አብዛኞቹ የአውሮጳ ህብረት ሀገራት ቢሆኑም ሁሉም አንድ ናቸው አንልም ግን የሚሉትን እንጠብቃለን ባሳለፍነው ጊዜ በሰብአዊ መብት ጥሰት ረገድ እኛን ለመውቀስ ሲሰራ እንደነበረም አይዘነጋም ሲሉ አምባሳደሩ በመግለጫቸው ተናግረዋል።

በቤቴልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *