
የደቡብ አፍሪካው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ “The Words of A President: Jacob Zuma Speaks” የተሰኘዉ አዲሱ መጽሃፋቸዉን ይፋ አድርገዋል።ጃኮብ ዙማ የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው የተጠረጠሩበትን የሙስና ወንጀል የሚመረምር ኮሚሽን ፊት ለመቅረብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተነሳ ጥፋተኛ በማለት ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ዙማ አዲሱን መጽሃፋቸዉን ይፋ ያደረጉት በጤና እክል ምክንያት ከእስር ከተለቀቀ ከወራት በኋላ ነው።እ.ኤ.አ በ2018 ዙማ ከስልጣን የለቀቁት የሚቀርብባቸዉ ክስ ተከትሎ ጫና እየጨመረባቸዉ መምጣቱን ተከትሎ ነው።
የዙማ ቃል አቀባይ ምዝዋኔሌ ማንኒ መፅሃፉ በሽያጭ ረገድ ክብረ ወሰን እንሚይዝ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ተደምጠዋል።ጋዜጠኛ ካሪን ማጉን ኒውስዴይ ፕሮግራም እንደተናገረችዉ መፅሃፉን በትክክል የፃፉት የቀድሞው ፕሬዝዳንት አይመስሉም ብላለች።
ከመጽሃፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ዙማ ከፍርድ ቤት ጋር ተያይዞ ያለባቸዉን ህጋዊ መጪዎች ለመክፈል ይዉላል ተብሏል፡፡
በስምኦን ደረጄ