መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 5፤2014-ያልተከተቡ መንገደኞችን የሚያሳፍሩ አየር መንገዶችን እቀጣለሁ ስትል ጋና አስጠነቀቀች

የጋና ባለስልጣናት እንደተናገሩት አየር መንገዶች ያልተከተቡ የውጭ ሀገር ዜጎችን ወደ ሀገር ውስጥ ይዘዉ በሚመጡት ላይ በአንድ መንገደኛ 3,500 የአሜሪካን ዶላር እንደሚቀጡ አስታዉቀዋል፡፡አየር መንገዶች የመንገደኞችን አስፈላጊውን የጤና መግለጫ ቅጽ መሙላታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው ተብሏል።

ከዛሬ ማክሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው አዲሱ መመሪያ የኮቪድ-19 ኦሚክሮን ልዉጥ የቫይረሱን ስርጭትን ለመግታት ያለመ ነው።የኮሮና ቫይረስ ክትባት ባልወሰዱ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ላይ እገዳውን ለማጠናከር መመሪያዉ ተግባራዉ ሆኗል፡፡

የጋና ዜጎች እና በጋና የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ከእገዳው ነጻ ናቸው፣ ነገር ግን በአውሮፕላን ማረፊያው ለመስተናገድ እንደሚታገዱ ተሰምቷል፡፡የጋና ባለሥልጣናት በበዓል ወቅት እየጨመረ የመጣው የኢንፌክሽን ስጋት እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል ።

ጋና ከ30 ሚሊዮን ህዝቧ ውስጥ ከ10 በመቶ በታች እስካሁን ክትባት ሰጥታለች።ጋና በሚቀጥለው ወር ክትባቱን መዉሰድ ለመንግስት ሰራተኞች ፣ ለጤና ባለሙያዎችን እና ለተማሪዎች አስገዳጅ እንደሚሆን አስታዉቃለች፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *