
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የህወሓት ቡድኑ በሰሜን ሸዋ ዞንበተለያዩ አካባቢዎች ላይ ያደረሰው ውድመት ከፍተኛ መሆኑን በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት መጋቢ ሃዲስ ቀሲስ ነቃ ጥበብ አባቡ ከብስራት ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል። በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ላይ በቡድኑ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ስለመሆኑ አንስተዋል።
ከፍተኛ የሚባል ጉዳት ከደረሰባቸው መካከልም በደብረ ሲና ጊዮርጊስ እንዲሁም መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን እንዲሁም በጣርማበር መሶቢት ገብርኤል፣ በካራቆሬ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ተጠቃሽ ሲሆን አሁንም ድረስ የጉዳቱ መጠኑን የማጣራት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያም አሁን ካለችበት ጭንቅ እንድትወጣ፤ እንዲሁም ህይወታቸውን ላጡ ደግሞ ጸሎተ ፍትሃት እንዲሆን በማሰብ ከታህሳስ አምስት ጀምሮ ለሶስት ቀናት የቆየው የምህላ ጸሎት እሮብ እለት መጠናቀቁን መጋቢ ሃዲስ ቀሲስ ነቃ ጥበብ አባቡ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በኤደን ሽመልስ