መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 7፤2014-በደብረ ብርሃን ከተማ ከ120 በላይ የኦነግ ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ

በደብረ ብርሃን ከተማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጁት የኦነግ ሸኔ እና የህውሃት ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ እየተደረገ እንደሚገኝ ተነግሯል ፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በከተማዋ መግቢያ እና መውጫ ኬላዎች እንዲሁም ደግሞ አጠናክሮ እያደረጋቸው በሚገኙ የቤት ለቤት ፍተሻዎች አማካይነት የሽብር ቡድኑ አባላትን እንቅስቃሴ መግታት እየተቻለ እንደሚገኝ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የቴክኒክና ሙያ ልማት ኢንተርፕራይዝ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አካሉ ወንድሙ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ።

እስከ አሁን ባለው ሂደት 124 የኦነግ ሸኔ አባላትን ጨምሮ ከ3ሺኅ በላይ የብሬን ጥይቶች እንደተያዙ ሃላፊው ገልፀዋል ፡፡

የብሬን ጥይቶቹ ሆነ ተጠርጣሪዎች ኬላ ላይ እና በከተማዋ ውስጥ በተደረገው የተጠናከረ ፍተሸ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያነሱት ሃላፊው እነዚሁ ተጠርጣሪዎች ለሚመለከተው የፀጥታ አካል ተላልፈው እንደተሰጡ ተናግረዋል ፡፡

በአሁን ሰዓት የከተማ አስተዳደሩ ሆነ መላው የፀጥታ መዋቅሩ ሰርጎ ገቦች እና ፀጉረ ልውጦች ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ያሉት ሃላፊው ይህ ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ ከተማይቱ አስተማማኝ ሰላም እንድታገኝ ይደረጋል ብለዋል ፡፡

ናትናኤል ሀብታሙ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *