መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 7፤2014-የቆጣሪ አንባቢ በመምሰል ቤት ለቤት በመዘዋወር ሲዘርፉ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጋምቤላ ከተማ የቆጣሪ አንባቢ በመምሰል ቤት ለቤት በመዘዋወር ሲዘርፉ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የጋምቤላ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ድርጊቱ የተፈፀመው በጋምቤላ ከተማ ኒው ላንድ ሰፈር ሲሆን፤ ተጠርጣሪዎቹ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መያዛቸውን በጋምቤላ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ ደግአረገ መንግስት ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎ ህብረተሰቡ ቆጣሪ አንባቢዎች ለንባብ በሚመጡበት ወቅት የተቋሙን መለዮ ልብስ እና የተቋሙ ሰራተኛ መሆናቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ወይም ባጅ የያዙ መሆናቸውን ሳያረጋግጡ ወደቤታቸዉ ማስገባት እንደሌለባቸዉ አቶ ደግአረገ አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም ህብረተሰቡ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ጥፋትና ውድመት የሚያደርሱ እና መሰል ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ግለሰቦችን ሲመለከት ለፀጥታ ኃይሎች ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን ማድረግ አለበት ሲሉ አቶ ደገረግ መንግስት ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *