መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 8፤2014-አሸባሪው ህወሓት በኮምቦልቻ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ሶስት መጋዘኖችን ላይ ዝርፊያ መፈጸሙ ተሰማ

አሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት የኮምቦልቻን ከተማ በወረራ ይዞ በቆየበት ቀናት ዉስጥ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ብር በመሰብሰብ ለሀገር ልማት በማዋል የበኩሉን አስተዋጽኦ ሲያደርግ በነበረው የኮምቦልቻ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ላይ ከፍተኛ ውድማት ማድረሱ ተገልጿል፡፡

መዳረሻውን ጥፋት አድርጎ ተግባሩን እያሳየ የሚገኘው የሽብር ቡድኑ በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሶስት መጋዘን ዉስጥ የነበሩ ንብረቶችን ሙሉ ለሙሉ ከመዝረፉም በላይ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን ማውደሙን የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰማን ዳውድ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን ከማውደሙም በላይ የግብር ከፋዮችን እና የሰራተኛውን ማህደር እና ሰነድ ከጥቅም ውጭ ቡድኑ አድርጓል፡፡በአሁኑ ሰዓት ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ወደ ቀድሞ ስራ ለመግባት የተለያዩ ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ እና በቀጣይም የወደሙ ንብረቶችን በዝርዝር እንደሚያሳውቅ የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰማን ዳውድ ለጣቢያችን ጨምረዉ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *