መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 8፤2014-የትራንስፖርት የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሆነ !

የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ መደረጉን የቢሮው የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ይርጋለም ብርሃኔ ለብስራት ተናግረዋል፡፡

የከተማ ትራንስፖርት ቢሮው የታሪፍ ማሻሻያ በማጥናት የትራንስፖርት ዘርፏ ላይ አገልግሎት ሰጪዎች ጥያቄንና ማህበረሰቡን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የታሪፍ ማሻሻያው ተግባራዊ ሆኗል።

ከታህሳስ 8 ጀምሮ እውን በሚሆነው የታሪፍ ማሻሻያ በሚዲ ባስ ታክሲ(ሀይገር እና ቅጥቅጥ ባሶች)በኪሎ ሜትር 40ሳ የነበረው ወደ 45ሳ ከፍ ተደርጓል። በከተማ ሚኒባስ ታክሲ በፊት ከነበረው በኪሎ ሜትር 90ሳ ወደ 1ብር በሰው ከፍ እንዲል ሁኗል።

ይህም ማለት በአዲሱ ታሪፍ መሰረት በሚዲ ባሶች 1ብር ዝቅተኛው ከፍተኛው 2ብር ፣ በከተማ ሚኒባስ ታክሲ ከ50ሳንቲም ከፍተኛው እስከ 3ብር ከ50 ሳንቲም ጭማሪ ተደርጓል።
የከተማ አስተዳደሩ ድጎማ የሚያደርግ በመሆኑ ፤
የታሪፍ ጭማሪው የብዙሃን ትራንስፖርት ማለትም (አንበሳ፣ሸገር፣ፐብሊክ ባስ) የመሳሰሉትን አያካትትም።

በከተማዋ በጥቅሉ እስከ 10,000 የሚጠጉ አገልግሎት መስጪያዎች ሲኖሩ ፤ በሁሉም የትራንስፖርት አገልግሎቶች በድግምግሞሽ ከ 2.6ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ያጓጉዛሉ። ህገወጥ የመስመር ማቆራረጥ ፣ አለመሸፈንና የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉት አገልግሎት ሰጪዎችን በሚመለከት ከ350በላይ የቁጥጥር ባለሙያዎች አሉ ተቀናጅተው እንዲሰሩ ይደረጋል ድንገተኛና መደበኛ ቁጥጥር ይደረጋል ከፍተኛ ቅጣት ይኖረዋል ተብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ በየቀኑ ከ 300 በላይ ተሽከርካሪዎች ይቀጣሉ። በየቀኑ የሚቀጣው የተሽከርካሪ መጠን ቁጥር ቀደም ካሉት ጊዜያት ጨምሯል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *