መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 11፤2014-የቀድሞ የተማሪዎች መብት ተሟጋች ጋብሪኤል ቦሪች የቺሊ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸነፉ

በቺሊ በፀረ መንግስት ተቃውሞ ወቅት ከፍተኛ ታዋቂነትን ያተረፉትና የግራ ክንፍ የመወሰኛው ምክር ቤት አባል የሆኑት ጋብሪኤል ቦሪች የቺሊ ፕሬዝዳንት በመሆን ተመርጠዋል።99 በመቶ የመራጮች ድምፅ የተቆጠረ ሲሆን ጋብሪኤል ቦሪች በ56 በመቶ የመራጮችን ድምፅ ያገኙ ሲሆን ዋንኛ ተቀናቃኛቸው የወግ አጥባቂው እጩ ጆሴ አንቶኒዮ ካስት 44 በመቶ የመራጮችን ድምፅ አግኝተዋል።

ካስት ሽንፈታቸው ይፋ መደረጉን ተከትሎ በትዊተር ገፃቸው ላይ የራሳቸውንና የቦሪችን ፎቶ በማድረግ ታላቅ ድል እንኳን ደስ አለህ ሲሉ አጋርተዋል።በ35 ዓመታቸው ቀጣዩ የቺሊ መሪ መባል የቻሉት ጋብሪኤል ቦሪች በሀገሪቱ ታሪክ በእድሜ ትንሹ ፕሬዝዳንት ለመባል በቅተዋል።

ተሰናባቹ ፕሬዝዳንትና ወግ አጥባቂው ቢሊየነር ሴባስቲያን ፒኔራ በስልጣን ሽግግር ወቅት መንግስታቸው ሙሉ ድጋፍ ለቦሪክ እንደሚሰጥ በቪዲዮ ኮንፍረንስ ላይ ተናግረዋል።ቦሪክ ከፒኔራ ገር ባደረጉት የቪዲዮ ኮንፍረንሱ ላይ የቺሊውያን ሁሉ ፕሬዝዳንት እሆናለሁ ሲሉ ተናግረዋል።ይህንን ፈተና ለመወጣት የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ ብለዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *