
አንዲት ሴት ወታደር በስራ ላይ እያለች የታገቢኛለሽ የጋብቻ ጥያቄን በመቀበሏ በቁጥጥር ስር መዋሏን የናይጄሪያ ጦር ሰራዊት ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡“የናይጄሪያ ጦር የመከላከያ ልብስ ለብሳ ከፍቅር ግንኙነት ጋር የተያያዘ ጉዳይ መፈጸሟ የወታደሩን የስነ ምግባር ደንብ ጥሳለች” ሲሉ አክለዋል።
ከፊት ለፊቷ ተንበርክኮ ቀለበት በመያዝ የታገቢኛለሽ ጥያቄ ላቀረበላት ፍቅረኛዋ በእሺታ ስትቀበል የሚያሳይ ቪዲዮ ባለፈው ሳምንት መሰራጨቱ ተነግሯል፡፡የሴት የመብት ተሟጋች ድርጅቶች በበኩላቸዉ በወታደሩ ላይ የተወሰደዉ እርምጃ አድሎ አለበት ሲሉ ከሰዋል።
ሙሉ ወታደራዊ ዩኒፎርም በለበሱ ወንድ ወታደሮች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ሲወሰድ አልተመለከትንም ሲል የሴቶች ማጎልበት እና የህግ ድጋፍ ቡድን ገልጿል።የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንታዊ እጩ ኦሞዬሌ ሶዎር የሰራዊቱን ውሳኔ “አሳሳቢ” ሲሉ አውግዘዋል።
በስምኦን ደረጄ