መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 12፤2014-3 ቦምቦች ይዘው የተገኙ የኦነግ ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ

በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ደገም ወረዳ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 2 የሸኔ ቡድን አባላት ከታጠቁት የጦር መሳሪያ ጋር በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

በደገም ወረዳ ኢላሙ ሚካኤል በተባለ አካባቢ አንድ ቦታ መሽገው የሽብር ተግባር ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት የሸኔ ቡድን አባላት ከታጠቁት የጦር መሳሪያ ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ መሆኑን የደገም ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ሀሰን አልዬ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ግለሰቦቹ የአሸባሪው ቡድን ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ወደ ከተማው በመግባት በአመራር አካላት እና በህብረተሰቡ ላይ ጥቃት ለማድረስ ዝግጅት ላይ እንደነበሩ የተናገሩት ኢንስፔክተሩ ሶስት ቦምቦች እና ሁለት ክላሽኮቭ መሳሪያ ከበርካታ ጥይቶች ጋራ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በወንጀል ድርጊት ተጠርጥረው የሚፈለጉት ግለሰቦቹ የአሸባሪው ቡድን ቅጥረኛ ሆነው የሽብር ተግባር ላይ መሰማራተቸው መረጋገጡን ኢንስፔክተር ሀሰን አልዬ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *