መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 13፤2014-በሞጆ ከተማ አንድ ግለሰብ ነፍሰጡር ባለቤቱን እና ሁለት ልጆቹን ገድሎ ራሱን አጠፋ❗️

በሞጆ ከተማ ነዋሪ የነበሩት አቶ ገዛኸኝ ተሾመ እና ፋቲያ አልዬ የ20 አመት እና የ13 አመት ሁለት ልጆችን አፍርተዉ በትዳር ተጣምረው ለዓመታት ኖረዋል፡፡

ከዚህ በፊት ሁለት ትዳር የነበራቸዉ ገዛህኝ ተሾመ በተለያዩ ጊዜያት ትዳራቸዉን ከፈቱ በኃላ ከወ/ሮ ፋቲያ አልዬን ጋር በመጣመር በሞጆ ከተማ 02 ቀበሌ ቀጠና 6 ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ህዳር 28 ቀን 2014 ከምሽቱ 1:30 ገደማ ባልታወቀ ምክንያት የስድስት ወር ነፍሰ ጡር ባለቤቱን እና ሁለት ልጆቹን በመግደል ራሱን አጥፍቷል ።

ፓሊስ ባደረገው ምርመራም ግለሰቡ በስሙ በተመዘገበ የክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያ የስድስት ወር ነፍሰጡር ባለቤቱን እና ሄርሜላ ገዛኸኝ የተባለች የ 20 አመት ሴት ልጁን እንዲሁም አብዲያ ገዛኸኝ የተባለ የ13 አመት ወንድ ልጁን ገድሎ ራሱን ማጥፋቱን የሞጆ ከተማ መስተዳድር ፖሊስ ጽህፈት ቤት የወንጀል ምርመራና ፍትህ ማሰጠት የስራ ሂደት ባለቤት ኢንስፔክተር እንግዳ ተሾመ ከብስራት ሬድዮ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *