ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ቶታል አካባቢ በዛሬው እለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ፣ቁጥራቸው በውል ባልተገለፁ ሰዎች ላይ የከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረስ ተገልጿል፡፡
በትራፊክ አደጋው ሰባት የቤት መኪኖች ፣አንድ ሞተር እና ሸገር አውቶቡስ መጋጨታቸው ተነግሯል። አውቶቡስ አቅጣጫውን የሳተ ሲሆን የደረሰው አደጋ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ብርሀኑ ኩመ ለብስራት ሬዲዮ ተናረዋል፡፡
በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች ከመንገዱ እስኪነሱ ድረስ ተዘግቶ የነበረው መንገድ አሁን ክፍት መሆኑ ተገልጿል።
በሳምራዊት ስዩም