መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 13፤2014-በካማሺ ዞን በጸረ-ሠላም ኃይሎች ታፍነው የነበሩ 62 ሰዎች ወደ ማህበረሰቡ ተቀላቀሉ

በቤኒሻንጉል ክልል ካማሺ ዞን በጸረ-ሠላም ኃይሎች ታፍነው የነበሩ 62 ሰዎች የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ባካሄዱት አሰሳና ኦፕሬሽን ከጠላት እጅ ወጥተው ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀላቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የአሰሳና የኦፕሬሸን ስራውን የመሩት የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ምስጋና እንጂፋታ እንደገለጹት፣ ለሃገርና ለወገን ደንታ የሌላቸው የአሻባሪው ህወሓት ተላላኪዎች ማህበረሰቡን በማታለል፣ በማስገደድና በማፈን ላልተገባ ዓላማ እያሰለፏቸው ነው።

የታፈኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን የጸጥታ ኃይሉ ከፀረ-ሰላም ኃይሎች እጅ ለማስለቀቅ ለተደረገው ትግል አመስግነው፥ ንጹሃንን ከጠላት የመነጠል ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

ቀሪ በየአካባቢው በግዳጅ የታፈኑ ሰዎች በሠላማዊ መንገድ ወደ መንግሥት እንዲመጡ መንግስትም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደረግላቸው መገለፁን ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳይ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *