መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 14፤2014-በጅማ ከተማ 32 ሀሰተኛ ማህተሞች እና የተለያዩ ማስረጃዎች ይዞ የተገኘው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በጅማ ከተማ መስተዳድር ወረዳ 02 ውስጥ 32 የተለያዩ ተቋማት ሀሰተኛ ማህተሞች እና ማስረጃዎች ይዞ የተገኘው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የከተማው ፖሊስ አስታዉቋል፡፡ተከሳሹ ተረፈ ዘውዴ የሚባል ሲሆን በመኖሪያ ቤቱ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ሀሰተኛ የትምህርት እና የመንጃ ፍቃድ ማስረጃዎች በቁጥጥር ስር መዋሉን የጅማ ከተማ ወረዳ 2 ፖሊስ ፅ/ቤት የወንጀል ምርመራ እና ፍትህ ማስፈፀም የስራ ሂደት ሀላፊ ዋና ሳጅን ብርሃኑ አባፊጣ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በግለሰቡ እጅ 32 የተለያዩ ተቋማት ማህተሞች፣ኮምፒተሮች ፣ፕሪንተሮች፣መያዛቸው ተገልጿል፡፡የወረዳዉ ፖሊስ ምርመራ በማድረግ በቁጥጥር ስር በማዋል ክስ መስርቷል፡፡የክስ መዝገቡን ለጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በማቅረብ ተከሳሹ በአንድ ዓመት እስራት እንዲቀጣ ዉሳኔ ተላልፎበታል፡፡

የጅማ ከተማ መስተዳድር ፖሊስ ፅ/ቤት ዳይሬክተር ኮማንደር ፉፋ መገርሳ በሀሰተኛ ማስረጃዎች የተነሳ የተለያዩ ተቋማት ችግር ውስጥ መግባታቸውን የገለፁ ሲሆን በተለይ ባንኮችና መሰል የፋይናንስ ተቋማት ከብድር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *