መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 20፤2014-በቦረና ዞን ከሚገኙ ተማሪዎች 11 በመቶ የሚሆኑት በትምህርት ገበታቸው አልተገኙም ተባለ

በቦረና ዞን በ2014 የትምህርት ዘመን ከተመዘገቡ ተማሪዎች መካከል አስራ አንድ በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ አለመገኘታቸውን የጋዮ ፓስተሮሊስት ዲቨሎፕመንት ኢንሼቲቭ አስታውቋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በዝናብ እጥረት ሳቢያ በተፈጠረው የድርቅ አደጋ በዞኑ በ2014 ዓ.ም ከተመዘገቡ 124ሺ 330 ተማሪዎች ውስጥ አስራ አንድ በመቶዎቹ ትምህርታቸውን ማቋረጣቸውን የጋዮ ፓስተሮሊስት ዲቨሎፕመንት ኢንሼቲቭ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መሰለ ስዩም ለብስራት ሬድዮ ተናረዋል፡፡

የወደፊት ተስፋ የሆኑ ተማሪዎቹን የተከሰተውን ድርቅ መቆጣጠር እና መርዳት ካልተቻለ በቀጣይም ተጨማሪ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሊያቋርጡ የሚችሉበት አጋጣሚ ሰፊ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ያቋረጡት በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ተፈናቃዮቹ አካባቢውን በመልቀቃቸው እና ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት መሄድ ባለመቻላቸው መሆኑን አቶ መለሰ ጠቁመዋል፡፡ በቦረና ዞን ከአራት መቶ ሰማንያ ሺ በላይ ሰዎች በምግብ እጥረት ላይ ይገኛሉ፡፡

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *