መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 20፤2014-በፈረንሳይ ከ179ሺ በላይ ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ሪፖርት ተደረገ

በአውሮጳ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ይገኛል። በአውሮጳ በሚገኙ ሀገራት በኦሚክሮን የኮሮና ቫይረስ ልውጥ አዲስ ዝርያ የሚጠቁ ሰዎች እየጨመረ ባለበት በዚህ ጊዜ ፈረንሳይ በቫይረሱ የሚጠቁ ሰዎች በከፍተኛ ፍጥነት መጨመሩን ይፋ አድርጋለች።

በትላንትናው እለት ብቻ በፈረንሳይ 178,807 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸው ሪፖርት ተደርጓል።የፈረንሳይ የጤና ሚኒስትር ኦሊቪየር ቫራን በጥር ወር የመጀመሪያ ቀናት በቀን እስክ 250ሺ ሰዎች በቫይረሱ ሊጠቁ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዣን ካስቴክስ አዳዲስ እንቅስቃሴን የሚገድቡ ህጎች እንደሚተገበሩ ይፋ አድርገዋል።በሳምንት ከስራ ቀናት መካከል ቢያንስ ሶስት ቀናት ከቤት ውስጥ ሆኖ መስራት አስገዳጅ እንደሚደረግም ተናግረዋል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *