ባለፉት ስድስት ወራት የማህጸን መውጣት ችግር ያጋጠማቸው 600 እናቶች የቀዶ ህክምና ማግኘታቸውን በጤና ሚኒስቴር የእናቶች ጤና ኦፊሰር ወ/ሮ እቴነሽ ገ/ዮሃንስ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። የዚህን ያህል አገልግሎት መስጠት ቢቻልም በተፈለገው መጠን ለመስራት የበጀት እጥረት እንቅፋት መሆኑን አንስተዋል።
ለተከታታይ አመታት በተለያዩ ምክንያቶች ወጥ በሆነ መልኩ መቀጠል ባይቻልም የግብአት ድጋፎችን ከተለያዩ ድርጅቶች በመቀበል አገልግሎቱን በመስጠት እናቶችን ለማዳን እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።ህክምናው በሀምሊን ፌስቱላ ማዕከል በኩል እየተሰጠ ነው ያሉት ወ/ሮ አለምነሽ በማህጸን መውጣት ችግር ዙሪያ የግንዛቤ እጥረት በመኖሩ እናቶች ወደ ህክምና ማዕከል ከመምጣት ይልቅ በራሳቸው መፍትሄ ለመውሰድ እየሞከሩ በመሆናቸው ለእናቶች እንዲሁም በሆስፒታል ለሚገኙ ባለሙያዎች ግንዛቤ መፍጠር ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
ከዚህ ቀደም ህመሙ ያለባቸው እናቶች በገንዘብ ሲታከሙ የቆዩ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ህክምናውን በነጻ በመሰጠት ላይ እንገኛለን ያሉት ወ/ሮ አለምነሽ፡በበጀት እጥረቱ ምክንያት በሚፈለገው መጠን አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ አልቻልንም ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።
ቤተልሄም እሽቱ