መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 21፤2014-በህንድ ጎዋ ውስጥ በክርስቲያኖ ሮናልዶ ምስል የታነጸዉ ሀዉልት ዉዝግብ አስነሳ

ለእዉቁ የእግር ኳስ ተጫዋች ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አዲስ ሃውልት በህንድ ጎዋ ግዛት ዉስጥ መታነጹ ውዝግብ አስነስቷል፣ ነዋሪዎቹ የህንድ ተጫዋቾችን ዘንግቶ ለፖርቹጋላዊው የእግር ኳስ ተጫዋች ክብር መሰጠቱን ተቃውመዋል።

የጎዋ ግዛት ሚኒስትር ሚካኤል ሎቦ በትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት ሃውልቱ እግር ኳስን እንደ ስፖርት ለማስተዋወቅ እና ወጣቶች ጨዋታውን እንዲጫወቱ ለማነሳሳት የተሰራ ነው ሲሉ ለዉዝግቡ ምላሽ ሰጥተዋል።ሰዎች ስለ እግር ኳስ ሲያወሩ ስለ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ይነሳል። ስለዚህ ይህን ሃውልት እዚህ ላስናቆም በታዳጊ ወንዶች እና ልጃገረዶች መነሳሳት ይፈጥራል በተጨማሪም የእግር ኳስ ጨዋታ ፍቅር እያደገ ይሄዳል ሲል ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን ይበሉ እንጂ 400 ኪሎ ግራም የሚመዝነዉ ሃውልት በጎዋ ግዛት ዋና ከተማ ፓናጂ በተመረቀ ማግስት ጥቁር ባንዲራ የያዙ ተቃዋሚዎች በቦታው በመሰብሰብ የተቃዉሞ ድምጻቸዉን አስምተዋል፡፡ተቃዋሚዎቹ ለውጭ እግር ኳስ ተጫዋች ክብር መሰጠቱ ብቻ ሳይሆን ያበሳጫቸዉ አውሮፓዊቷ ሀገር ፓርቹጋል ጎዋን ለዘመናት በቅኝ ግዛትነት በመያዝ የተነሳም ነዉ፡፡

ሮናልዶ በጎዋ ስላለው ሐውልት በይፋ አስተያየት አልሰጠም።በህንድ ክሪኬት ተወዳጅ ስፖርት ሲሆን፣ እግር ኳስ በአንዳንድ አካባቢዎች እንደ ጎዋ ባሉት የበለጠ ተወዳጅነት አለው።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *