መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 21፤2014-በኢትዮጵያ በ104 ሚሊዮን ብር የተቋቋመው የአቮካዶ ዘይት ፋብሪካ ስራ ተጀመረ

ዋይቢኤም አቮካዶ ዘይት ፋብሪካ በሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በመቶ አራት ሚሊዮን ብር በይርጋለም ግብርና ማቀነባበርያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተቋቋመው ነው። ዘይቱን ወደ ወጪ የሚልከው ፋብሪካው ከአርባ ሺህ ገበሬዎች ጋር ትስስር ፈጥሯራ።ከአርሶ አደሮች የቀተበውን አቮካዶ ወደ ዘይት በመቀየር ወደ አውሮፓ እንደሚልክ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ አበባ ተመን ለብሰራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ለገበሬዎቹ ስራ እድል ከመፍጠሩም ባሻገር የውጭ ምንዛሬ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ፋብሪካው ስራ ከጀመረ ሁለት ሳምንት ሲያስቆጥር አሁን ላይ ለ50 ሠራተኞች በቋሚነት እንዲሁም አቅርቦት ላይ ለሚሰሩ መቶ ሃምሳ ሠራተኞች በጊዜያዊነት የስራ ዕድል መፍጠሩን አስታውሰው በቀጣይ ለአምሰት መቶ ሠራተኞች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

ፋብሪካው የአካባቢውን ማህበረሰብ ለመጥቀም ሲባል ምርቱን የሚያመርቱትን ሠራተኞች ከለቀማ ጀምሮ እስከ ማሽን ኦፕሬተር ድረስ የአቮካዶ ምርቱን የሚያቀርቡት የገበሬ ልጆች መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

የፋብሪካው ስራ መጀመር ለአካባቢው አርሶ አደሮች ቋሚ ገቢ መፍጠር የቻለ ሲሆን ምንም ዓይነት ግብዓት ከወጪ ማስገባት ሳያስፈልግ የወጪ ምንዘሬን በማስገኘት ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ላይም የሚያበረክተው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

በይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ3ዓመት በፊት ስራ የጀመረው ሳንቫዶ የአቮካዶ ዘይት ፋብሪካ ከ88ሺህ አርሶ አደሮች ጋር ትስስር በመፍጠርና ምርቱን በመሰብሰብ ለግብዓትነት ተጠቅሞ ያመረተውን የዘይት ምርት ወደ ኔዘርላንድ እየላከ ሲሆን በጊዜያዊነት ለ150 ሰዎች እና ለ40 ሰዎች ደግሞ በቋሚነት የስራ ዕድል ፈጥሯል ሲሉ ወ/ሮ አበባ ጨምረው ተናግረዋል።

በቤተልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *