መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 21፤2014-የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት የሼልን የነዳጅ ዘይት ፍለጋ አገደ

የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ግዙፉ የነዳጅ ኩባንያ ሼል በሀገሪቱ ምስራቃዊ የባህር ጠረፍ አካባቢ ለነዳጅ እና ለጋዝ ፍለጋ የሚያደርገውን ሙከራ አቁሞ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ እንዲታገድ ወሰነ።የነዳጅ ዘይት ለማግኘት የሚደረገዉ ሙከራ የሚያስከትለዉ የድምጽ ፍንዳታ የባህርን ህይወት ይጎዳል ብለው በሚሰጉ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች ውሳኔውን አድንቀዋል።

ሼል ስራዎችን ለአፍታ ለማቆም መፈደዱን አስታዉቋል፡፡የደቡብ አፍሪካ የኢነርጂ ሚኒስትር ግዌዴ ማንታሼ የፕሮጀክቱን ተቺዎች በተመለከተ አፍሪካ የሃይል ሃብቷን እንዳትጠቀም ይፈልጋሉ ሲሉ አውግዘዋል።በምስራቅ ኬፕ ግዛት ውስጥ የሚገኘዉ 250 ኪ.ሜ የባህር ዳርቻ በተፈጥሮ ውበቱ እና በባህር ዉስጥ ሀብት ይታወቃል።

ነዳጅ ፍለጋ እንዲቆም ዘመቻ የሚያደርጉ ቡድኖች በርካታ የባህር ውስጥ ፍጥረታት ዶልፊኖች ጨምሮ እንደሚጎዱ ይከራከራሉ፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *