መደበኛ ያልሆነ

ታህሳስ 22፤2014-????አጫጭር መረጃ ከዓለም ዙሪያ ኮቪድን በተመለከተ

????????በሩሲያ ባለፉት 24 ሰዓት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የ926 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ቫይረሱ በሩሲያ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ ከ307ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡በቫይረሱ የሚጠቁ ሰዎች ብዛት በሞስኮ ከተማ ብቻ 50 በመቶ ጨምሯል፡፡

????በዓለም ዙሪያ ባለፉት ሰባት ቀናት ከ7.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮቪድ መጠቃታቸዉ ሪፖርት ሲደረግ ይህም ማለት በየቀኑ በአማካይ 1,045,000 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸዉ ተገልጿል፡፡

????????በስፔኑ ሀያል ክለብ ባርሴሎና ቡድን ውስጥ የተረጋገጠ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ብዛት ወደ 10 ከፍ ብሏል ፣ ይህም ቡድኑ ወደ ሊግ ጨዋታ መመለሱን አደጋ ላይ የሚጥል እንደሆነ ተገልጿል፡፡የላሊጋው ተቀናቃኙ የአትሌቲኮ ማድሪድ አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኔ እና የፊት መስመር አጥቂዉ ግሪዝማንን ጨምሮ አምስት ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡

????????የፊንላንድ የቀድሞ ፕሬዝዳንት እና የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ማርቲ አቲሳሪ ለሁለተኛ ጊዜ በኮቪድ 19 ተጠቅተዉ ሆስፒታል መግባታቸዉን በመርቲ አቲሳሪ ስም የተመሰረተዉ ፋውንዴሽን አስታውቋል ።

????????የህንድ ሙምባይ ከተማ የኮቪድ ስርጭት መጨመሩን ተከትሎ ቅዳሜ ለሚጀምረዉ 2022 ዓመት የአዲስ ዓመት ድግሶች እና ከአራት በላይ ሰዎች የሚሰበሰቡበት ስብሰባ መታገዱን የመንግስት ባለሥልጣናቱ አስታዉቀዋል፡፡

????????በቻይና ከተማ ዢያን የሚኖሩ ነዋሪዎች የምግብ እጥረት ቅሬታ አሰሙ፡፡ ምንም እንኳን የቤጂንግ መንግስት በአሁኑ ጊዜ በቂ አቅርቦት እንዳሉ ቢገልጽም ነዋሪዎች ቅሬታቸዉን ገልጸዋል፡፡በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መጨመር የተነሳ የ13 ሚሊዮን ሰዎች መኖሪያ በሆነችዉ ዢያን ከተማ እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ ታግዷል፡፡

????????በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ አፍና አፍንጫን መሸፈን ከአርብ ጀምሮ አስገዳጅ እንደሚሆን ተነገረ፡፡ይህንን መመሪያ ባላከበሩ ሰዎች ላይ የ135 ዩሮ ወይም 153 ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

????????በአሜሪካ በ24 ሰዓት ዉስጥ በክብረ ወሰን ደረጃ የተመዘገበ የኮቪድ ተጠቂዎች ሪፖርት ተደረገ፡፡ በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ482,400 በላይ ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸዉ ሪፖርት ሲደረግ ባለፉት ሰባት ቀናት በአማካኝ 301 ሺ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *